ጎህ ባንክ በ1.2 ቢሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታል ተመሠረተ

በምሥረታ ላይ ከሚገኙ ባንኮች መካከል ጎህ ቤቶች ባንክ ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችለውን መሥራች ጉባዔ ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

ከሌሎች ባንኮች በተለየ በቤት ግንባታና በባንክ ንግድ ሥራዎች ላይ በማተኮር እንደሚንቀሳቀስ በማስታወቅ አክሲዮን በመሸጥ ላይ የቆየዉ ጎህ ባንክ ወደ ሥራ ለመግባት ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ አግኝቶ የመሥራች ጉባዔ ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

ባንኩ እንዳስታወቀው በ530 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታልና በ1.2 ቢሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታል በይፋ ተመሥርቷል፡፡

Source :- https://www.gohbetochbanksc.com/

Want to say something? Post a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Compare